ከፍተኛ ሊግ | የካ ሁለት ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአሰልጣኙን ውል አድሷል

የካ ክፍለ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የስምንት ነባሮችን እና የአሰልጣኙን ውል ማደሱን አስታውቋል።

በ2011 ደካማ አጀማመር ካደረገ በኋላ በሁለተኛው ዙር አቋሙን በማሻሻል በሊጉ መቆየት የቻለው የካ ክፍለ ከተማ በዚህ ዓመት ተጠናክሮ ለመቅረብ እንቀስቃሴ የጀመረ ሲሆን ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል። በ2011 በኢኮስኮ ቆይታ ያደረጉት የቀኝ መስመር ተጫዋቹ ሙሴ ተክለወይኒ እና ተከላካዩ ተስፋዬ ሃይሶ ለቡድኑ የፈረሙ አዲስ ተጫዋቾች ሆነዋል።

የዋና አሰልጣኙ ባንተይርጋ ጌታቸውን ውል ያራዘመው ክለቡ የስምንት ነባር ተጫዋቾችን ውል ማደሱን አሳውቋል። ሀይማኖት ሰይፉ፣ አዩብ ዘይኑ፣ ንጉስ ጌታሁን፣ ደምሰው ቦጋለ፣ ምናልካቸው ፋንጮ፣ አሸናፊ ምትኩ፣ አንተነህ ከተማ እና መሀሪ ዮሴፍ ውል ያደሱ ተጫዋቾች ናቸው።


© ሶከር ኢትዮጵያ