ሰበታ ከተማ ግብጠባቂ ለማስፈረም ተቃርቧል

ጋናዊው ግብጠባቂ ዳንኤል አጄይ አዲስ አዳጊው ሰበታ ከተማን ለመቀላቀል ተቃርቧል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት ከጅማ አባጅፋር ጋር ድንቅ የሚባል ቆይታ የነበረውና ቡድኑ በ210 የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ እንዲያነሳ የጎላ ድርሻ የነበረው ጋናዊው ዳንኤል አጄይ የእግር ኳስ ህይወቱን በሃገሩ ክለብ ሌበሪቲ ፕሮፌሽናልስ በመጀመር ለደቡብ አፍሪካው ፍሪ ስቴት ስታርስ ጨምሮ ለመዳማ እና ለታንዛንያው ሲምባ መጫወት የቻለ ሲሆን መጨረሻ ምዕራፍ ላይ የደረሰውን ሰበታ ከተማ ዝውውር በቀጣይ ቀናት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ቀደም ብለው አሰልጣኝ ውበቱ አባተን በመቅጠር የበርካታ ተጫዋቾች ዝውውር ያጠናቀቁት ሰበታዎች በቀጣይ ቀናትም ተጫዋች ያስፈርማሉ ተብሎ ሲጠበቅ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውም በአዳማ ከተማ ጀምረዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ