ደደቢት የምክትል አሰልጣኝ ቅጥር ፈፀመ

አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊትን ዋና አሰልጣኝ አድርገው በመቅጠር በርካታ ተጫዋቾች ያስፈረሙት ደደቢቶች አሰልጣኝ ፀጋዝአብ ባህረጥበብን ረዳት አሰልጣኝ አድርገው ቀጥረዋል።

ባለፉት ዓመታት በብሄራዊ ሊጉ ክለብ ትግራይ ውሃ ስራዎች በዋና አሰልጣኝነት የሰራው ይህ አሰልጣኝ ከዚህ በፊት በዘጠናዎቹ መጨረሻ መቐለ 70 እንደርታን ማሰልጠኑ ሲታወስ በተጫዋችነት ዘመኑም ትራንስ ኢትዮጵያ እና በአንድ ወቅት በክልሉ በርካታ ዋንጫዎች ያነሳው መብራት ኃይል በተከላካይነት ተጫውቷል።

በሌላ ዜና ለዋናው ቡድን ግብዓት የሚሆን ወጣት ቡድን ለማዋቀር በዝግጅት የሚገኙት ደደቢቶች በመቐለ ዩንቨርስቲ አሪድ ሜዳ ለበርካታ ወጣት ተጫዋቾች የሙከራ ዕድል ማዘጋጀታቸው ሲታወቅ ምልመላውም ለቀጣይ ቀናት እንደሚቀጥል ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ