ኢትዮጵያ ቡና የመስመር ተከላካይ ለማስፈረም ተስማማ

ኢትዮጵያ ቡና አንዳርጋቸው ይላቅን የክለቡ አስራ ሶስተኛ ፈራሚ ለማድረግ ተስማምቷል፡፡

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወጣት ቡድን ያደገውና በፍነጥት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ አማካኝነት ተካቶ የነበረው የቀኝ መስመር እና የመሐል ተከላካዩ አንዳርጋቸው ይላቅ ከፈረሰኞቹ ከለቀቀ በኋላ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታትን በአዳማ ከተማ በመጫወት አሳልፏል።

መስከረም 5 በአዲስ አበባ ዝግጅትን የጀመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በአሁኑ ሰአት በዝዋይ (ባቱ) ከተማ በመክተም በአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ እና ምክትሉ ዘላለም ፀጋዬ እየተመሩ ልምምዳቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ