ከፍተኛ ሊግ | አክሱም ከተማ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል

አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሀዬን የቀጠረው አክሱም ከተማ ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾች ማስፈረም ችሏል።

ግብጠባቂው ማቲዮስ ሰለሞን (ከነቀምቴ ከተማ)፣ በተከላካይ ስፍራ ላይ የሚጫወቱት ዘነበ ቱታ (ከነቀምቴ ከተማ) እና ዘላለም በረከት (ከወልዲያ)፣ አማካዮቹ ኢዩኤል መላኩ (ከኢኮስኮ)፣ እንዳለማው ታደሰ (ከፌዴራል ፖሊስ) ሳሙኤል ተስፋዬ እና ንስሀ ታፈሰ (ከስሑል ሽረ) እንዲሁም አጥቂው አንተነህ ተሻገር (ከወሎ ኮምበልቻ) እና በሀላባ ቆይታው የ2009 የከፍተኛ ሊጉ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ የነበረው ዘከሪያስ ፍቅሬ (ከሀምበሪቾ) ወደ አክሱም ከተማ ያመሩ ተጫዋቾች ሆነዋል።

በተያያዘ ቡድኑ የስምንት ተጫዋቾች ውል ሲያድስ በቅርቡ ተጨማሪ አዳዲስ ተጫዋቾች ቡድኑን እንደሚቀላቅሉ ክለቡ አሳውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ