ሴካፋ ከ20 ዓመት በታች| ኤርትራ ሦስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቀቀች

የቀይ ባህር ግመሎች ሱዳንን በማሸነፍ ሦስተኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።

ላለፉት ሦስት ሳምንታት በዩጋንዳ አዘጋጅነት የተካሄደው እና ከጥቂት ሰዓታት በኃላ ፍፃሜውን የሚያገኘው የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ከሰዓታት በፊት በኤርትራ እና በሱዳን መካከል በተደረገ የደረጃ ጨዋታ ሲቀጥል ኤርትራ በቢንያም መንግስትአብ ብቸኛ ግብ ሱዳንን አሸንፋለች።

በዋናው ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዓለምሠገድ ኤፍሬም ላለፉት ዘጠኝ ወራት ዝግጅት ያደረጉት ኤርትራዎች በውድድሩ በርካታ ግቦች በማስቆጠር ቀዳሚ ሲሆኑ ከቀናት በፊትም በአምስት ተጫዋቾች መጥፋት የብዙዎችን ትኩረት መሳባቸው ይታወሳል።

ውድድሩ ከጥቂት ሰዓታት በኃላም ሲቀጥል በፍፃሜው ኬንያ እና ታንዛንያ ይገናኛሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ