ሰበታ ከተማ ወጣት ግብ ጠባቂ አስፈረመ

ሰበታ ከተማ ወጣቱ ግብ ጠባቂ ፋሲል ገብረሚካኤልን አስፈርሟል፡፡

በዳሽን ቢራ የታዳጊ ቡድን እግርኳስን የጀመረው ይህ ግብ ጠባቂ ከክለቡ መፍረስ በኋላ ወደ ደደቢት ተስፋ ቡድን አምርቶ የተጫወተ ሲሆን በሰማያዊዎቹ ቤትም ባሳየው ብቃት ለኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን መጠራትም ችሏል፡፡ ባለፈው ዓመት በከፍተኛ ሊጉ አክሱም ከተማ ቆይታ የነበረው ፋሲል የሰበታ ከተማ አዲስ ተጫዋች በመሆን ለሁለት ዓመታት ፊርማውን አኑሯል፡፡

ከስምንት አመታት በኋላ ወደ ፕሪምየር ሊጉ የተመለሰው ሰበታ ከተማ የ2012 የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በአዳማ ከተማ እየሰራ ይገኛል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ