ሎዛ አበራ በመጀመሪያ ጨዋታዋ ግብ አስቆጠረች

የማልታውን ክለብ ቢርኪርካራን በቅርቡ መቀላቀል የቻለችው ሎዛ አበራ በአዲሱ ክለቧ የመጀመርያ ጨዋታ ሁለት ጎሎችን አስቆጥራለች።

ስምንት ክለቦችን የሚያሳትፈው የ2019/20 የማልታ የሴቶች የመጀመሪያ ዲቪዚዮን ትላንት ምሽት በይፋ ተጀምሯል፡፡ በ2018/19 የውድድር ዘመን የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻለው ቢርኪርካራ ትላንት ምሽት 2:00 ሰአት በሜዳው ቻርለስ አቤልታ ስታዲየም የቅርብ ተቀናቃኙ ሄበርኒያስን አስተናግዶ 8-0 ሲረመርም ሎዛ አበራ አስር ቁጥር በመልበስ በመጀመሪያው አሰላለፍ ውስጥ ተካታ ተጫውታለች። ከተቆጠሩ ጎሎች መካከልም በ18ኛው እና 87ኛው ደቂቃ ሁለት ግቦችን በስሟ አስመዝግባለች። ቀሪዎቹን ጎሎች ሄበርኒያሶች ሁለት ግቦችን በራሳቸው ላይ ሲያስቆጥሩ ካይሊ ዊልስ ሁለት ግብ፣ ራኒያ ጉስቲ እና ማሪያ ስኪቢራስ ደግሞ አንድ አንድ ጎል ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ሆነዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ