ኢትዮጵያ ቡና ከመስመር ተከላካዩ ጋር ተለያየ

ባለፈው የውድድር ዓመት ኢትዮጵያ ቡናን ከተቀላቀሉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረው ተካልኝ ደጀኔ ከቡናማዎቹ ጋር ተለያይቷል።

በአርባ ምንጭ ከተማ፣ ደደቢት እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተሳኩ ዓመታትን ካሳለፈ በኋላ በ2011 የውድድር ዘመን ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀለው የግራ መስመር ተከላካዩ ተካልኝ ደጀኔ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ቀሪ ኮንትራት እያለው የሙከራ ዕድል በመሰጠት አቅሙን ማየት አለብኝ ማለቱን ተከትሎ ነው በሀሳቡ ባለመስማማት ከቡድኑ ጋር በስምምነት ሊለያይ የቻለው።

በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ለኢትዮጵያ ቡና በመጫወት ጥሩ የውድድር ዘመን የጀመረው ተካልኝ በፕሪምየር ሊጉ በርከት ባሉ ጨዋታዎች ላይ መሳተፍ ችሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ