መቐለዎች የአማካይ ተጫዋች ዝውውር አጠናቀቁ

ባለፈው ዓመት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ቆይታ ያደረገው አማካዩ ዳንኤል ደምሴ ወደ መቐለ 70 እንደርታ አምርቷል።

ባለፈው የውድድር ዓመት ጥሩ አጀማመር አድርጎ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ የተመረጠው አማካዩ በተለይ በአሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜስ ቀዳሚ ተመራጭ የነበረ ሲሆን በርካታ አማካዮችን ካስፈረመው ቡና ጋር ባሳለፍነው ሳምንት መለያየቱ ይታወሳል።

ከዚህ ቀደም በወልዲያ እና ባህር ዳር ከተማ መጫወት የቻለው አማካዩ ቀደም ብሎ ከቡድኑ ጋር ልምምድ መስራት የጀመረ ሲሆን ሐይደር ሸረፋ እና ጋብሬል አህመድን የመሳሰሉ የአማካይ ክፍል ተጫዋቾች ላጣው ቡድን ጥሩ ግብዓት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ