ኢትዮጵያ ቡና ከመከላከያ ጋር የተለያየውን አማካይ አስፈረመ

ኢትዮጵያ ቡናዎች ከቀናት በፊት ከመከላከያ ጋር በስምምነት የተለያየው የአማካይ ሥፍራ ተጫዋቹ ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃንን አስፈርመዋል።

የቀድሞው የኤሌክትሪክ ተጫዋች ፍቅረየሱስ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለቆ ወደ ወደ ሀዋሳ ከተማ ካመራ በኋላ ከቡድኑ ጋር በሁለት የውድድር ዓመታትን መልካም እንቅስቃሴ ማድረጉ ይታወሳል። ከወራት በፊት ለመከላከያ ለመጫወት ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም ቡድኑ በከፍተኛ ሊግ እንደሚሳተፍ በመረጋገጡ ከቡድኑ ጋር በስምምነት የተለያየው ተጫዋቹ ለኢትዮጵያ ቡና ለሁለት ዓመት መፈረሙ ተረጋግጧል።


© ሶከር ኢትዮጵያ