ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ወጣት ተጫዋቾችን አስፈረመ

በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ለዘንድሮ የውድድር ዓመት ማስፈረም የቻለው ኢትዮጵያ ቡና የሁለት ወጣት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል።

አማካዩ ነቢል ኢብራሂም ከፈረሙት መካከል ነው። ነቢል በ2007 በአዲስ አበባ ከተማ ተስፋ ቡድን መጫወት ሲችል በኋላም በ2009 በአሰልጣኝ ሥዩም ከበደ የአሰልጣኝነት ዘመን በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለዋናው ቡድን በቢጫ ቲሴራ መጫወት ችሏል። ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ደግሞ በከፍተኛ ሊግ ከየካ ክ/ከተማ ጋር መልካም ጊዜ በማሳለፍ ለመጪው የውድድር ዘመን ለኢትዮጵያ ቡና ለመጫወት የፊርማውን አኑሯል።

ኢብራሂም ባአዱ ሌላው የቡድኑ አዲስ ፈራሚ ነው። የተከላካይ አማካዩ ኢብራሒም በ2007 በደደቢት ተስፋ ቡድን መጫወት ሲችል በመቀጠል በቡራዩ ከተማ፤ ዓምና ደግሞ በከፍተኛ ሊጉ የካ ክ/ከተማ ጥሩ ግልጋሎትን ሲሰጥ ቆይቶ ወደ ኢትዮጵያ ቡና የሚቀላቅለውን ስምምነት ፈፅሟል።

ሁለቱም ተጫዋቾች ለቅድመ ዝግጅት ወደ በባቱ ከተማ ካቀናው ቡድን ጋር አብረው በመግባት ጠንካራ ስራ መስራት ከጀመሩ ሰነባብተዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ