ሎዛ አበራ ጎል ባስቆጠረችበት ጨዋታ ቢርኪርካራ አሸንፏል

ሎዛ አበራ በአራት ጨዋታዎች አምስተኛ ጎሏን ስታስቆጥር ቡድኗ ቢርኪርካራም በመሪነቱ ቀጥሏል።

በአራተኛ ሳምንት የማልታ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ቢርኪርካራዎች ተጋጣሚያቸው ስዌቂ ዩናይትድን 4-1 ማሸነፍ ችለዋል። ሎዛ አበራ በጨዋታው አንድ ግብ በማስቆጠር የሊግ ጎሎቿን አምስት አድርሳለች። ቀሪዎቹን ጎሎች ደግሞ ስቴፋንያ ፋሩግያ፣ ትሬሲ ቱማ፣ ራንያ ጒስቲ ማስቆጠር ችለዋል።

የዛሬው ድል ከቢርኪርካራ በእኩል ሰባት ነጥብ በጎል ልዩነት ተበልጦ ሁለተኛ በነበረው ስዌቂ ዩናይትድ ላይ መሆኑን ተከትሎ ቡድኑ ተከታዮቹን በሶስት ነጥብ በልጦ በዘጠኝ ነጥብ በአንደኛነት ተቀምጧል።

የማልታ ፕሪምየር ሊግ ከሃያ ስድስት ቀናት በኃላ በአምስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች እንደሚቀጥል ሲታወቅ ቢርኪርካራዎች ከሜዳቸው ውጭ በአቤላ ስቴድየም ሞስታን ይገጥማሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ