ካሜሩን 2021| አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል

አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ በመጪው ኅዳር ወር መጀመሪያ በቀናት ልዩነት ከማዳጋስካር እና አይቮሪኮስት ጋር ላለባቸው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅት ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል፡፡

በዚህ ጥሪ ውስጥ የኢትዮጵያ ቡናው ሁለገብ ተጫዋቾች አስራት ቱንጆ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጠራ የቡድን አጋሩ አቡበከር ናስር ከጉዳት መልስ ቡድኑን ተቀላቅሏል። በተመሳሳይ በቅርቡ ሀዲያ ሆሳዕናን የተቀላቀለው ይሁን እንደሻው በ2008 በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከተካሄደው የሴካፋ ውድድር በኋላ ዳግም ጥሪ የደረሰው ተጫዋቾች ሆኗል፡፡

ዋልያዎቹ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ በመቐለ ከተማ በመሰባሰብ ልምምዳቸውን የሚጀምሩ ይሆናል፡፡

የተመረጡ ተጫዋቾች ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች (3)፡ ምንተስኖት ዓሎ (ስሑል ሽረ)፣ ለዓለም ብርሀኑ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ተክለማርያም ሻንቆ (ኢትዮጵያ ቡና)

ተከላካዮች (7) አህመድ ረሺድ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ አስቻለው ታመነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ አንተነህ ተስፋዬ (ሰበታ ከተማ)፣ ረመዳን የሱፍ (ስሑል ሽረ)፣ ደስታ ደሙ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ መሳይ ጳውሎስ (ሀዋሳ ከተማ)፣ አስራት ቱንጆ (ኢትዮጵያ ቡና)

አማካዮች (10) ከነዓን ማርክነህ (አዳማ ከተማ)፣ ዮናስ በርታ (አዳማ ከተማ)፣ ሀይደር ሸረፋ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ፉአድ ፈረጃ (አዳማ ከተማ)፣ አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ)፣ ታፈሰ ሰለሞን (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ይሁን እንደሻው (ሀዲያ ሆሳዕና)፣ ጋቶች ፓኖም (ሀራስ ኤል ሆዳድ/ግብፅ)፣ ሽመልስ በቀለ (ምስር አል መቃሳ/ግብፅ)

አጥቂዎች (5) ቢኒያም በላይ (ስሪያንስካ/ስዊድን)፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤል (መቐለ 70 እንደርታ)፣ መስፍን ታፈሰ (ሀዋሳ ከተማ)፣ አዲስ ግደይ (ሲዳማ ቡና)፣ አቡበከር ናስር (ኢትዮጵያ ቡና)


© ሶከር ኢትዮጵያ