የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ተራዘመ

በመጪው ቅዳሜ ሊጀመር የነበረው አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ በዕለቱ እንደማይጀመር ሲረጋገጥ በአራት ቀናት ተገፍቶ እንደሚካሄድ ታውቋል።

የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ እንዳስታወቀው ፌዴሬሽኑ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ባደረገው ምክክር ውድድሩ ለቀናት እንዲራዘም ከስምምነት ተደርሷል። በዚህም መሠረት ሐሙስ ጥቅምት 27 ቀን 2012 እንደሚጀምር ተገልጿል።

የ14ኛው የአዲስ አበባ ዋንጫ አስቀድሞ ከጥቅምት 22 እስከ ኅዳር 7 ድረስ ለማካሄድ ታስቦ እንደነበረ የሚታወስ ነው።

የመክፈቻ ጨዋታዎች 

ሐሙስ ጥቅምት 27 ቀን 2012
09:00 | ባህር ዳር ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ

11:00 | ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መከላከያ

* አዳዲስ መረጃዎች በኤዲት ተካተውበታል


© ሶከር ኢትዮጵያ