የከፍተኛ ሊግ የዝውውር መስኮት ጥቅምት 25 ይዘጋል

የከፍተኛ ሊግ ተሳታፊዎች ምዝገባ እንዲሁም የዝውውር መስኮት የፊታችን ማክሰኞ ይጠናቀቃል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከዚህ ቀደም በሚሰራበት አሰራር መሠረት የዝውውር መስኮቱ ውድድሩ ከተጀመረ ከሦስት ሳምንታት በኋላ የሚዘጋ ሲሆን ከዘንድሮ ጀምሮ ቀነ ገደብ ማስቀመጥ ችሏል። በዚህም ሐምሌ 26 ተከፍቶ የነበረውና ላለፉት ሦስት ወራት ክፍት ሆኖ የቆየው የከፍተኛ ሊግ ዝውውር መስኮት ጥቅምት 25 የሚጠናቀቅ መሆኑ ተገልጿል።

በተያያዘ ዜና የከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ ቡድኖች የመመዝገብያ እና የሚጠበቅባቸውን ክፍያ የሚያጠናቅቁበት የጊዜ ገደብ እንደ ዝውውር መስኮቱ ሁሉ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ድረስ እንደሚቆይ ታውቋል።

የ2012 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ከፕሪምየር ሊጉ የወረዱ ሦስት ቡድኖች እና ከአንደኛ ሊግ ያደጉ ስድስት ቡድኖችን ጨምሮ በ36 ተሳታፊዎች መካከል በሦስት ምድቦች ተከፍሎ ይካሄዳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ