ትውልደ ኢትዮጵያዊው የአውስትራሊያውን ክለብ ተቀላቀለ

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ተከላካይ ፊልሞን አሰፋ በሰሜን አውስትራሊያ ሊግ ለሚወዳደረው ክሮይዶን ኪንግስ ለመጫወት በትናንትናው ዕለት ፌርማውን አኑሯል።

ከዚህ በፊት በሰሜን አውስትራሊያ ሊግ ለሚወዳደረው አደላይድ ኮሜትስ ሲጫወት የቆየው ይህ ተከላካይ ከአንጋፎቹ አንቶኒ ትሪምቦሊ፣ ጆን ሃል እና ሉክ ክሊሞክ እና ሌሎች ቀጥሎ ወደ ቡድኑ የተቀላቀለ ስምንተኛ ተጫዋች ነው።

ክለቡ ከዚህ ቀደም ሌላው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ተከላካይ ያሬድ አብተው እና ኤርትራውያኖቹ ዓለማየሁ ከበደ እና አምባሳደር ዮሴፍ የተጫወቱበት ክለብ ሲሆን ቀጣይ የውድድር ዓመት በአውስትራልያ ሰሜን ሊግ የሚወዳደሩ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ