ከፍተኛ ሊግ | ባቱ ከተማ የአሰልጣኙን ውል ሲራዝም አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ

የ2011 የአንደኛ ሊግ ቻምፒዮን በመሆን ወደ ከፍተኛ ሊግ ያደገው ባቱ ከተማ የክለቡን ዋና እና ረዳት አሰልጣኝ ጨምሮ የነባሮችን ውል ሲያድስ አስራ አንድ አዳዲስ ተጫዋቾችንም አስፈርሟል፡፡

ክለቡ አምና ወደ ከፍተኛ ሊጉ እንዲያድግ የረዱት ዋና አሰልጣኙ ቁፋ ኮርሜ እና ረዳት አሰልጣኙ ቱሉ ደስታን ውል ያራዘመ ሲሆን የአስራ አራት ነባር ተጫዋቾችንም ውል አራዝሟል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከተለያዩ ክለቦች አስራአንድ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡

ክለቡን የተቀላቀሉት ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡-
በለጠ ተስፋዬ (ግብ ጠባቂ ከአ/አ ከተማ)፣ ክብረት ታደሰ (ተከላካይ ከቡራዩ ከተማ)፣ ክንዱ ባየልኝ (ተከላካይ ከኮፈሌ)፣ ምንተስኖት አበራ (አማካይ ከአርሲ ነገሌ)፣ ክንዳለም ፍቃዱ (አማካይ ከቡራዩ)፣ በክር ከድር (አማካይ ከሞጆ ከተማ)፣ የሺጥላ ዳቢ (የመስመር አጥቂ ከአርሲ ነገሌ)፣ አቤል ሀብታሙ (የመስመር አጥቂ ከጅማ ሸነን ጊቤ/ኦሮሚያ ሊግ)፣ ሱራፌል አየለ (የመስመር አጥቂ ከለገጣፎ ለገዳዲ)፣ ያሬድ ወንድማገኝ (አጥቂ ከኮፈሌ ከተማ) እና ይሁን ደጀኔ (አጥቂ ከአሰላ ከተማ)


© ሶከር ኢትዮጵያ