2021 አፍሪካ ዋንጫ | ዝሆኖቹ ስብስባቸውን ይፋ አድርገዋል

አሰልጣኝ ኢብራሂም ካማራ ኢትዮጵያ እና ኒጀርን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የሚገጥመው ስብስባቸውን ይፋ አደረጉ።

ለካሜሩን አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከኢትዮጵያ ፣ ኒጀር እና ማዳጋስካር የተደለደሉት ዝሆኖቹ ከሳምንታት በኋላ ኒጀር እና ኢትዮጵያን የሚገጥመው ስብስባቸውን ይፋ ሲያደርጉ በፓርማ እንደ አዲስ የተወለደው ጀርቪንሆ አሁንም በብሄራዊ ቡድኑ መካተት አልቻለም። በአንፃሩ የአርሰናሉ ኒኮላ ፔፔ፣ የክሪስታል ፓላሱ ዊልፍሬድ ዛሃ፣ የቶትንሃሙ ሰርጂ ኦርዬ እና የኤሲ ሚላኑ ፍራንክ ኬሲ ኢትዮጵያን በሚገጥመው ስብስብ ተካተዋል።

ባልተለመደ መልኩ በርካታ በአፍሪካ የሚጫወቱት ተጫዋቾች ያካተተው የዝሆኖቹ ስብስብ ይህንን ይመስላል።

ግብ ጠባቂዎች፡ ቦሆው ሲልቭያን፣ ባድራ ዓሊ፣ ሳዮባ ማንዴ

ተከላካዮች፡ ኮናን ጋስልያን፣ ሰርጄ ኦርዬ፣ ብሪቶ ዌሊ፣ ካኖን ዌልፍሬድ፣ ትሬመር ኢስማዒል፣ ኮማራ ቼክ፣ ዎንሎ ኩሊባሊ፣ ደሊ ሲሞን

አማካዮች፡ ፍራንክ ኬሲ፣ ሃቢብ ማይጋ፣ ሴኮ ፎፋና፣ ቪክቶርየን አንጋባን፣ ኮሜ ኮፊ ክርስትያን

አጥቂዎች: ማክስ ግራዴል፣ ኒኮላ ፔፔ፣ ዊልፍሬድ ዛሃ፣ ቦሊ ዮሃን፣ ያኩ ሜይቴ፣ አሳሌ ሮጀር


© ሶከር ኢትዮጵያ