የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች ቅሬታ ማሰማታቸውን ቀጥለዋል

ነገ በሚጀምረው የአዳማ ከተማ ዋንጫ ላይ ስምንት የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች እንደማይጫወቱ ታውቋል።

ከደሞዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ ተደጋጋሚ ቅሬታ እያቀረቡ የሚገኙት የክለቡ ነባር ስምንት ተጫዋቾች “ከቡድኑ ጋር ዝግጅት እየሰራን ብንቆይም ለወራት ያልተከፈለን ደሞዝ እስካሁን ያልተከፈለን በመሆኑ ነገ በሚጀምረው የአዳማ ከተማ ዋንጫ ላይ የማንሳተፍ መሆኑን እያሳወቅን ለሚፈጠሩት ማንኛውም ችግሮች ተጠያቂ እንደማንሆን የሚመለከተው አካል ሁሉ ይወቅልን።” ሲሉ ለፌዴሬሽኑ ዛሬ ደብዳቤ አስገብተዋል።

አሰልጣኝ ዻውሎስ ጌታቸው የስምንት ተጫዋቾችን አገልግሎት ነገ ከአዳማ ከተማ ጋር በሚኖረው የመክፈቻ ጨዋታ ላይ የማያገኙ ቢሆንም በቀሩት የቡድኑ ተጫዋቾች ውጤታማ ለመሆን ጠንካራ ዝግጅታቸው እያደረጉ እንደሆነ ሰምተናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ