የትግራይ ዋንጫ ዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት የሚካሄድበት ቀን ታውቋል

ለሁለተኛ ጊዜ ለሚካሄደው የትግራይ ዋንጫ የእጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት በትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፅሕፈት ቤት ይከናወናል።

እስካሁን ድረስ ሰባት ተሳታፊዎችን ያሳወቀው ይህ ውድድር በቀጣይ ቀናት አንድ ተጨማሪ ተሳታፊን አክሎ በስምንት ክለቦች መካከል ይካሄዳል ተብሎ ሲጠበቅ ቀድሞ በወጣው መርሃግብር መሰረትም ውድድሩ እሁድ ጥቅምት 30 ይጀምራል።

በውድድሩ ተጋባዦቹ ሲዳማ ቡና እና ወላይታ ድቻ ጨምሮ የዓምናው አሸናፊ መቐለ 70 እንደርታ፣ ስሑል ሽረ፣ ደደቢት፣ አክሱም ከተማ እና ሶሎዳ ዓድዋ እንደሚሳተፉ ሲረጋገጥ በቀጣይ ቀናትም ስምንተኛ ተሳታፊ ቡድን ውድድሩን የሚቀላቀልበት ዕድል የሰፋ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ