የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባዔ የሚካሄድበት ቀን ታውቋል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔ በኅዳር ወር መጨረሻ እንዲካሄ መወሰኑን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም ጥቅምት 24 እንዲካሄድ ተወስኖ ኋላ ላይ በአንድ ሳምንት የተራዘመውና ኋላ ላይ ደግሞ በሀገር አቀፍ ስፖርት ምክርቤት ስብሰባ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመው ይህ ጠቅላላ ጉባዔ በመጪው ኅዳር 28 ቀን 2012 አዲስ አበባ ላይ እንደሚካሄድ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

የጠቅላላ ጉባዔ ቦታ ወደፊት እንደሚገለፅ ያስታወቀው ፌዴሬሽኑ አጀንዳዎችን ወደ ባለድርሻ አካላት እየላከ ሲሆን ከዚህ ቀደም ከተያዙት አጀንዳዎች መካከል የመተዳደርያ ደንብን የማሻሻል አጀንዳ እንዲወጣ መደረጉ ተያይዞ ተገልፃል፡፡

የጠቅላላ ጉባዔው አጀንዳዎች የሚከተሉት ናቸው


© ሶከር ኢትዮጵያ