ከፍተኛ ሊግ | ገላን ከተማ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል

በአሰልጣኝ ዳዊት ታደሰ እየተመራ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው ገላን ከተማ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾች ማስፈረም ችሏል።

ዐቢይ ቡልቲ ወደ ገላን ካመሩት መካከል ነው። የአጥቂ መስመር ተሰላፊው ዐቢይ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ መድን፣ ሰበታ ከተማ እና ወልዲያ ተጫውቶ ያሳለፈው ዐቢይ በ2011 ወደ ፕሪምየር ሊግ ባደገው ሰበታ ከተማ የግማሽ ዓመት ቆይታ አድርጓል።

አህመድ ጀማል ሌላው የገላን አዲስ ፈራሚ ነው። የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ናሽናል ሴሜንት አማካይ በ2011 በኢትዮ ኤሌክትሪክ በመጫወት አሳልፏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ