ከፍተኛ ሊግ | ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን አዳዲስ ተጫዋቾች ሲያስፈርም የአሰልጣኙን ውልም አደሰ

በአሰልጣኝ እዮብ ማለ እየተመራ ከአንደኛ ሊግ ወደ ከፍተኛ ሊግ በክረምቱ ያደገው ሰሜን ሸዋ ደብረብርሀን አዳዲስ ሰባት ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአሰልጣኞችንም ውል አድሷል፡፡

ደብረ ብርሀን በቅድሚያ ቡድኑን እየመሩ ወደ ከፍተኛ ሊጉ እንዲመለስ የረዱት ዋና አሰልጣኙ እዮብ ማለን ጨምሮ የረዳቶቹ ኤፍሬም ተስፋዬ እና ሙሉዓለም ታፈሰን ውል ለተጨማሪ ዓመት ያራዘመ ሲሆን በቡድኑ ውስጥ የነበሩት የአስራስምንት ነባር ተጫዋቾችን ውልም አድሷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሰባት አዳዲሶችን አስፈርሟል፡፡

ፍሰሀ ረዲ (ግብ ጠባቂ ከላስታ ላሊበላ)፣ ስንታየሁ ሸዋፈራው (ተከላካይ ደሴ ከተማ)፣ አብርሀም ተስፋ (ተከላካይ ደሴ ከተማ)፣ አብነት ተስፋ (ተከላካይ ካፋ ቡና)፣ ሙሉቀን ተስፋዬ (አማካይ ካፋ ቡና)፣ ማትያስ መኮንን (አማካይ ደሴ ከተማ)፣ ገናናው ብርሀኑ (የመስመር አጥቂ አ/አ ፖሊስ) ክለቡን በአዲስ መልክ የተቀላቀሉ ናቸው፡፡

ባለፈው ዓመት በአንደኛ ሊግ ተሳታፊ የነበረው ሰሜን ሸዋ ደብረብርሀን በባቱ በተካሄደው የማጠቃለያ ውድድር በመለያ ጨዋታ ወደ ከፍተኛ ሊጉ ማደጉ ይታወሳል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ