የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ?

የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማሮን አስመልክቶ የተለያዩ ጥያቄዎች እየተነሱ ይገኛል።

አዲስ በተዋቀረ ኮሚቴ የሚመራው የዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኀዳር 21 እንደሚጀመር በሰባት አባላት የሚመራው የውድድሩ የበላይ አካል “ዐቢይ ኮሚቴ” መገለፁ ይታወቃል።

ሆኖም ከየክልሉ የፀጥታ ማረጋገጫ መዘግየት እና ከሜዳ ዝግጅት ጋር በተያያዘ ውድድሩ አስቀድሞ በወጣለት መርሐግብር መሠረት ላይካሄድ ይችላል የሚል ጥርጣሬ በአንዳንድ አካላት ዘንድ እየተነገረ ይገኛል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሶከር ኢትዮጵያ ባደረገችው ማጣራት ሊጉ በተያዘለት መርሐግብር እሁድ እንደሚጀምርና ከነገ ጀምሮ ለሁሉም ክለቦች የውድድሩ ፕሮግራም እንደሚበተን ለማወቅ ችለናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ