እንየው ካሣሁን ጉዳት አጋጥሞታል

በኢትዮጵያ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታ ላይ ጉዳት ያስተናገደው የዐፄዎቹ የመስመር ተከላካይ እንየው ካሣሁን ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል።

ከወልዋሎ በዘንድሮ የውድድር ዓመት ፋሲል ከነማን መቀላቀል የቻለው ታታሪው የመስመር ተከላካይ በትናንቱ የአሸናፊዎች አሸናፊ የዋንጫ ጨዋታ ላይ በ39ኛው ደቂቃ ላይ አንገቱ አካባቢ በሚገኝ የእጅ ትከሻው ላይ ባጋጠመው ውልቃት በሰዒድ ሀሰን ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል።

በፍጥነት ለተሻለ ህክምና ወደ ቤተ-ዛታ ሆስፒታል የተላከው እንየው የትከሻ ውልቃቱ እንደተገጠመለት እና አሁን ጤንነቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል። ጉዳቱ ለቀናት በቂ እረፍት የሚያስፈልገው በመሆኑ ለተወሰኑ ጊዚያት ከሜዳ እንደሚርቅ ሰምተናል።

ይህን ተከትሎ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለአዲሱ ክለቡ አንድ ወይም ሁለት ጨዋታዎች ላይ አገልግሎት ላይሰጥ እንደሚችል ተገምቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ