ዋሊድ እና የሱፍ ዝውውር ሳያደርጉ የዝውውር መስኮቱ ተዘግቷል

 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመሃል ተከላካይ የሆነው ዋሊድ አታ እና የመስመር አማካዩ የሱፍ ሳላ ከትላንት በስቲያ በተዘጋው የዝውውር መስኮት ወደ ሌላ አዲስ ክለብ አለመዛወራቸውን ተጫዋቾቹ ለሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል፡፡ ዋሊድ ከቱርኩ ገንሰልበርሊጊ በስምምነት በታህሳስ ወር የተለያየ ሲሆን የሱፍ በኤፍሲ ዩናይትድ የነበረውን የአጭር ግዜ ውል አጠናቅቆ አዲስ ክለብ በመፈለግ ላይ ነው፡፡ የዝውውር መስኮቱ ቢዘጋም ሁለቱም ተጨዋቾች ክለብ አልባ በመሆናቸው ወደ መረጡት ክለብ መጓዝ ይችላሉ፡፡

በጉዳዩ ላይ ለሶከር ኢትዮጵያ አስተያየቱን የሰጠው “የሱፍ እስካሁን ወደየትኛው ክለብ አልተዛወርኩም፡፡ የተሻለ ውል የሚያቀርብልኝን ክለብ እየጠበቅኩ ነው” ብሏል፡፡

ተጫዋቾቹ ፈላጊ ክለብ እንዳላቸው ጨምረው ተናግረዋል፡፡ ዋሊድ እና የሱፍ በግላቸው ጠንካራ ልምምድ እያደረጉ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *