ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ይመራሉ

የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ሦስተኛ የምድብ ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ሲከናወኑ አንጎላ ላይ የሚደረገው ጨዋታ በኢትዮጵያውያን ዳኞች ይመራል።

የአንጎላው ፔትሮ ዲ ሎዋንዳ ከ ዩኤስኤም አልጀር የሚደርጉትን ይህን ጨዋታ በአምላክ ተሰማ በዋና ዳኝነት ሲመራው ረዳት ዳኞች ደግሞ ክንዴ ሙሴ እና ተመስገን ሳሙኤል እንዲሁም አራተኛ ዳኛ በላይ ታደሰ እንዲሆኑ ተመድበዋል።

ፔትሮ ሉዋንዳ ከዚህ ቀደም በቻምፒየንስ ሊጉ ማጣርያ ከዩጋንዳው ኬሲሲኤ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በላይ ታደሰ መምራቱ የሚታወስ ነው ።


© ሶከር ኢትዮጵያ