አራት የቀድሞ የሲዳማ ቡና ተጫዋቾች ቅሬታ አቀረቡ

ያለፉትን ሁለት ዓመታት ሲዳማ ቡና ሲያገለግሉ የቆዩ የቀድሞ አራት ተጫዋቾች ቅሬታቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

ቀደሞ ለሲዳማ ቡና ሲጫወቱ የነበሩና በዘንድሮ ዓመት ወደ ተለያዩ ክለቦች ያመሩት ፈቱዲን ጀማል፣ መሐመድ ናስር፣ ዳግም ንጉሴ እና ጫላ ተሺታ ናቸው ቅሬታቸውን ያሰሙት። ” ዓምና ቡድኑ ውጤታማ እንዲሆን ከሌሎች የቡድን አጋሮቻችን ጋር በመሆን ክለቡን ስናገለግል መቆየታችን ይታወቃል። ሆኖም ክለቡ በ2011 ሲጫወቱ ለነበሩ ተጫዋቾች እና ለአሰልጣኞች የገንዘብ ሽልማት ሲያበረክት እኛን በሽልማቱ አለማካተቱ ቅር አሰኝቶናል። የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ ሳሳሞን ለማግኘት በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም።” በማለት ቅሬታቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ሲዳማ ቡና የዐምናው ስኬታማ ውጤት ለማስመዝገቡ እና ዘንድሮ በትግራይ ዋንጫ ላይ የውድድሩ አሸናፊ ሆኖ በማጠናቀቁ ለክለቡ ተጫዋቾች እና ለአሰልጣኝኞች ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ባሳለፍነው ሳምንት ሽልማት ማበርከቱ ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ