መከላከያ በዓለምነህ ግርማ ላይ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ሆነ

ቀሪ የአንድ ዓመት ውል ከመከላከያ ጋር እያለው በክለቡ የስንብት ደብዳቤ የደረሰው የመስመር ተከላካዩ ዓለምነህ ግርማ ቅሬታውን ለፌዴሬሽኑ አሰምቶ ውሳኔን ቀደም ብሎ አግኝቶ የነበረ ሲሆን ክለቡ ውሳኔው አግባብ አይደለም በሚል ለፌዴሬሽኑ ይግባኝ ቢጠይቅም ውድቅ ተደርጎበታል፡፡

የመከላከያ ክለብ ለፌዴሬሽኑ ያስገባው የይግባኝ ደብዳቤ በበቂ ማስረጃ ተደግፎ የተወሰነ አይደለም፤ ይህም አግባብ ስላልሆነ ውሳኔው ይሻርልን፤ ክለቡ ያሰናበተው በመሆኑ ወደ ክለቡ መልሱት መባሉ አግባብ አይደለም። ስለዚህ ክፍያም ለመፈፀም አንገደድም የሚል ደብዳቤን ቢያስገባም የፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ የመከላከያን ጥያቄ ውድቅ በማለት በድጋሚ ውሳኔን ለተጫዋቾቹ ወስኗል፡፡

የውሳኔው ዝርዝር👇© ሶከር ኢትዮጵያ