ፕሪሚየር ሊግ ፡ አዳማ ከተማ የውድድር ዘመኑን የመጀመርያ ሽንፈት ሲያስመዘግብ ድሬዳዋ ከተማ ደረጃውን አሻሽሏል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ማጠቃለያ ጨዋታዎች ዛሬ ይርጋለም እና ድሬዳዋ ላይ ተደርገው ድሬዳዋ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል፡፡ ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡናን በሜዳው ነጥብ አስጥሏል፡፡

የከተማው ከንቲባን ጨምሮ ቁጥሩ ከፍተና የሆነ ተመልካች በተከታተለው ጨዋታ አዳማ ከተማን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ 2-0 አሸንፏል፡፡ የድሬዳዋን የድል ግቦች የ2007 የብሄራዊ ሊግ ከፍተኛ ግብ አግቢ በላይ አባይነህ በ40 እና 49ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡ በላይ ዘንድሮ ለብርቱካናማዎቹ ግብ ሲስቆጥር የመጀመርያው ነው፡፡

በጨዋታው 43ኛ ደቂቃ የድሬዳዋ ከተማው ሱራፌል ዳንኤል በቀይ ካርድ የተወደገ ሲሆን ሁለተኛውን አጋማሽ በ10 ተጫዋች ለመጫወት የተገደደው ድሬዳዋ ከተማ በተለይም 2ኛውን ግብ ካስቆጠረ በኋላ ውጤቱን ለማስጠበቅ አፈግፍጎ መጫወትን መርጧል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ አዳማ በ2008 የውድድር ዘመን የመጀመርያ ሽንፈቱን ሲያስተናግድ ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ2 ነጥቦች ዝቅ ብሎ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ ድሬዳዋ ከተማ ደግሞ 4 ደረጃዎችን አሻሽሎ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ይርጋለም ላይ ኤሌክትሪክን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና ካለግብ አቻ ተለያይቷል፡፡ ማራኪ እንቅስቃሴ ባልታየበት በዚህ ጨዋታ አድራሻ የሌላቸው ረጃጅም ኳሶች የጨዋታው ዋንኛ አካል ነበሩ፡፡

ሲዳማ ቡና አቻ መውጣቱን ተከትሎ ወደ ደረጃ ሰንጠረዡ የሚጠጋበትን እድል አበላሽቷል፡፡ በአንጻሩ ኤሌክትሪክ አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ የደረጃ ሰንጠረዡ ወገብ ላይ ተቀምጧል፡፡

የ9ኛ ሳምንት ውጤቶች

አርባምንጭ ከተማ 0-1 ቅዱስ ጊዮርጊስ

ዳሽን ቢራ 0-1 ደደቢት

ሀዋሳ ከተማ 1-0 ኢትዮጵያ ቡና

ወላይታ ድቻ 1-1 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ሀድያ ሆሳዕና 0-0 መከላከያ

ድሬዳዋ ከተማ 2-0 አዳማ ከተማ

ሲዳማ ቡና 0-0 ኤሌክትሪክ

የደረጃ ሰንጠረዡ ይህንን ይመስላል

standing

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከአንድ ሳምንት በኋላ የሚቀጥሉ ሲሆን በዚህ ሳምንት መጨረሻ የአፍሪካ የክለቦች ውድድሮች እና የኢትዮጵያ ሊግ ዋንጫ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

ከፍተኛ ግብ አግቢዎች ደረጃ

Untitled

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *