ቅዱስ ጊዮርጊስ ለእሁዱ የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ዝግጅት እያደረገ ነው

በ2016 የካፍ ቻምፒዮስ ሊግ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቦሌ ሚሌንየም አዳራሽ ጀርባ በሚገኘው የልምምድ ሜዳው ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡ 

በዛሬ ጠዋቱ የልምምድ ፕሮግራም አሰልጣኝ ማርት ኑይ ቡድኑን ለ3 ከፍለው ልምምድ ሲያሰሩ የነበረ ሲሆን በተሸጋሪ ኳሶች የማጥቃት እና የመከላከል ፣ ረጃጅም ኳሶችን የመጠቀም እንዲሁም በመስመር የማጥቃት ልምምዶችን ሲያሰሩ ተስተውሏል፡፡ ጠንካራ አካል ብቃት ልምምዶችም የዝግጅታቸው አካል ነበር፡፡

በልምምዱ ላይ ከጀርመን ህክምናውን አድርጎ ከተመለሰው ሳላዲን በርጊቾ እና በጉዳት ለ3 ወራት ከሚርቀው ብሪያን ኡሞኒ በቀር አዲሱ ፈራሚ ጎድዊን ቺካ እና ከክለቡ ጋር ልምምድ እያደረገ የሚገኘው ሳላዲን ሰኢድ ፣ ከጉዳት የተመለሱት በኃይሉ አሰፋ እና ምንያህል ተሾመን ጨምሮ ሁሉም ተጫዋቾች ልምምድ ሰርተዋል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከነገ ጀምሮ የልምምድ ቦታቸውን እሁድ ጨዋታ ወደሚያደርጉበት አዲስ አበባ ስታድየም የሚያዞሩ ሲሆን ነገ በ4፡00 ልምምዳቸውን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የ2016 የውድደር ዘመን ቅድመ ማጣርያ ቅዳሜ እና እሁድ በሚደረጉ ጨዋታዎች ሲጀመር ቅዱስ ጊዮርጊስ የሲሸልሱን ቻምፒዮን ሴይንት ሚሼል ዩናይትድ እሁድ በ10፡00 በአዲስ አበባ ስታድየም ያስተናግዳል፡፡

በክለቡ አጠቃላይ ዝግጅት ዙርያ ሶከር ኢትዮጵያ በመጪው አርብ ከተጫዋቾች እና አሰልጣኞች ጋር ቆይታ አድርጋ ወደ እናንተ ታደርሳለች፡፡

IMG_1589

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *