የኢትዮጵያ ሊግ ዋንጫ ፡ ፊሊፕ ዳውዚ ወደ ግብ ማስቆጠር ሲመለስ አዳማ ፣ ባንክ እና ሲዳማ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል 

በኢትዮጵያ ሊግ ዋንጫ የመጀመርያ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ቀሪዎቹ 3 ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡ አዳማ ከተማ ፣ ሲዳማ ቡና እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ወደ ሩብ ፍጻሜው የሚያሰሻግራቸውን ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

በ8፡00 አዲስ አበባ ስታድየም ላይ አዳማ ከተማ ከ ኤሌክትረክ ጋር ያደረጉት ጨዋታ በአዳማ ከተማ የመለያ ምቶች አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ አዳማ ከተማ ጫላ ድሪባ በ9ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ቀዳሚ ሲሆን አንተነህ ተሻገር በ69ኛው ደቂቃ ቀዮቹን አቻ አድርጓል፡፡ ጨዋታው 1-1 በመጠናቀቁ አሸናፊውን ለመለየት የመለያ ምቶች የተሰጡ ሲሆን አዳማ ከተማ 8-7 አሸንፎ ወደ ሩብ ፍፃሜው ተቀላቅሏል፡፡ በመለያ ምቶቹ ሱሌይማን መሃመድ ከአዳማ ፣ በረከት ተሰማ እና አወት ገብረሚካኤል ከኤሌክትሪክ አምክነዋል፡፡

IMG_1877

አበበ ቢቂላ ላይ በ8፡00 ዳሽን ቢራን የገጠመው ሲዳማ ቡና 1-0 አሸንፏል፡፡ ፈጣኑ የመስመር አማካይ አዲስ ግደይ የሲዳማ ቡናን የድል ግብ በ39ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ቀጥሎ በተካሄደው የንግድ ባንክ እና የድሬዳዋ ከተማ ጨዋታ ንግድ ባንክ በሰፊ ግብ አሸንፏል፡፡ ፊሊፕ ዳውዚ ወደ ግብ ማስቆጠር በተመለሰበት ጨዋታ ከባንክ የድል ግቦች ሁለቱን በ32 እና 90ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ቀሪዋን አንድ ግብ ደግሞ ተቀይሮ የገባው ሲሳይ ቶሊ አስቆጥሯል፡፡ አምና በ19 ግቦች የሊጉን ከፍተኛ ግብ አግቢነት በሁለተኝነት ያጠናቀቀው ፊሊፕ ዳውዚ ዘንድሮ ግብ ሲያስቆጥር ለመጀምርያ ጊዜ ነው፡፡

IMG_1949

የመጀመርያ ዙር ውጤቶች

አዳማ ከተማ 1-1 (8-7) ኤሌክትሪክ

ሲዳማ ቡና 1-0 ዳሽን ቢራ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3-0 ድሬዳዋ ከተማ

ኢትዮጵያ ቡና 0-0 (4-2) ሀድያ ሆሳዕና

አርባምንጭ ከተማ 1-0 ሀዋሳ ከተማ

መከላከያ ከ ወላይታ ድቻ (መከላከያ ባለበት የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ ምክንያት ጨዋታው ለሌላ ጊዜ ተላልፏል)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *