ደደቢት ሁለት ጋናዊያንን አስፈረመ

ደደቢት አንድ የተከላካይ አማካይ እና አንድ ተከላካይ ከጋና ማስፈረሙን አስታውቋል፡፡ ተከላካዩ ጆን ቱፎር ሲሰኝ አማካዩ ደግሞ ክዌሲ ካይል ይባላል፡፡

ከክለቡ የቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ ሚካኤል አምደ መስቀል እንዳገኘነው መረጃ ተጫዋቾቹ ለመጪዎቹ 2 የውድድር ዘመናት ለሰማያዊዎቹ ለመጫወት የተስማሙ ሲሆን በውድድር ዘመኑ የታየበትን ክፍተት ለመድፈን ይረዳዋል ተብሏል፡፡

ሶከር ኢትዮጵያ ዛሬ በክለቡ የልምመድ ስፍራ ተገኝታ እንደተመለከተችው የአማካዩ ክዌሲ አጨዋወት በክረምቱ ክለቡን ለቆ ለንግድ ባንክ የፈረመው ጋብሬል አህመድ ጋር ይመሳሰላል፡፡ ይህም በጋናዊው መልቀቅ ሳስቶ የነበረውን የአማካይ ክፍል ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የተከላከዩ ጆን ቱፎር መፈረምም በጉዳት የተቸገረውን ተከላካይ መስመር ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ክለቡ በአፍሪካ ውድድሮች ላይ ዳግም ተሳታፊ ለመሆን አላማን መያዙን የተናገሩት አቶ ሚካኤል የአዳዲስ ተጫዋቾቹ መፈረም አላማቸውን ለማሳካት እንደሚያግዛቸው ተስፋ አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለረጅም ጊዜያት መቋረጡን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ክለቦች ከውጭ ተጫዋች እንዲያስፈርሙ መፍቀዱ የሚታወስ ሲሆን ደደቢትን ጨምሮ ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ከውጭ ተጫዋቾችን ማስፈረም ችለዋል፡፡

ሁለቱ ተጫዋቾች የስራ ፈቃድ ጉዳያቸው በቶሎ ከተጠናቀቀ ደደቢት ከ ሀዋሳ ከተማ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ መሰለፍ ይችላሉ፡፡

IMG_1874

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *