ቅዱስ ጊዮርጊስ 3-0 ሴንት ሚሼል – ከጨዋታ በኋላ የተሰጡ አስተያየቶች 

በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ የመጀመርያ ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሲሸልሱን ሴንት ሚሸል 3-0 አሸንፏል፡፡ የሁለቱም ክለቦች አሰልጣኞች ጨዋታው መጠናቀቀ በኃላ አስተያየታቸውን ለጋዜጠኞች ሰጥተዋል፡፡

 

“ሴንት ሚሼል እግርኳስን ለመጫወት አልመጣም” ማርት ኖይ

 

ሰለጨዋታው ጨዋታው

” ጨዋታው ለኛ ከባድ ነበር፡፡ ምክንያቱም ተጋጣሚያችን እግርኳስን ለመጫወት አልመጣም፡፡ በስምንት እና ዘጠኝ ተጫዋቾች ይከላከሉ ነበር፡፡ በእንደዚህ ዓይነት የመከላከል አጨዋወት የሚጫወቱ ቡድኖች ላይ ክፍተት ማግኝት ከባድ ነው፡፡ እንደማስበው ጨዋታው ብዙ ውጣ ውረዶች የበዙበት ነበር፡፡ ”

በሁለተኛው አጋማሽ ተዳክሞ ስለታየው ቡድናቸው

” የሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ ለኛ መልካም አልነበረም፡፡ ተጫዋቾቼ በመልሶ ማጥቃት ግብ እንዳይቆጠርባቸው ስጋት ነበራቸው፡፡ የተጫዋች ቅያሪ ካደረግን በኃላ ወሳኝ ሶስተኛ ግብ ማስቆጠር ችለናል፡፡ ”

ከሁለት ሳምንት በኃላ ስለሚደረገው የመልስ ጨዋታ

“ከሴንት ሚሸል ጋር የምናደርገውን የመልስ ጨዋታ በትኩረትን ነው የምንመለከተው፡፡ ጨዋታውን የምናደረግበት ሜዳ የሰው ሰራሽ ሜዳ ስለሆነ ልምምዳችንን ሃዋሳ በሚገኘው የሰው ሰራሽ ሜዳ እናደርጋለን፡፡ ”

ስለክለቡ የቻምፒየንስ ሊግ ጉዞ

“የኛ እቅድ እስከቻለነው እና አቅማችን እስከቀደልን ድረስ በውድድሩ ላይ መጓዝ ነው፡፡”

IMG_0235

“በሲሸልስ የተለየ ውጤት ጠብቁ”  አንድሪው ጅያን ልዊ

 

ስለጨዋታው

“ጨዋታው ከዓየር ንብረቱ እና ካለው የቦታ ከፍታ እንፃር ከባድ ነበር፡፡ በውጤቱ አልተከፋሁም:; ምክንያቱም ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታው ማሸነፍ ይገባው ነበር፡፡ ከኛ የተሻለ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ”

ስለመልስ ጨዋታው

“በሲሸልስ የተለየ ውጤት ጠብቁ፡፡ በጉዳት ላይ የነበሩ ተጫዋቾች ወደ ቡድናችን ይመለሳሉ፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ብድንን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የገጠሙ ተጫዋቾችም አሉን፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ሲሸልስ ሲመጣ ጠንካራ ሆነን ነው የምንጠብቀው፡፡ በሃገራችን ላይ ግብ እናስቆጥራለን፡፡ ነገር ግን ነቅለን ወጥተን አናጠቃም ምክንያቱም ተጋጣሚያችን ጥሩ መልሶ ማጥቃትን መጠቀም የሚችል ቡድን አለው፡፡ ከዛሬው አሰላለፍ የተለየ አሰላለፍ በመልሱ ጨዋታ ይዘን እንቀርባለን፡፡ “

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *