ፌዴሬሽኑ ከእንግሊዝ እግርኳስ ማኅበር ጋር በጋራ የተዘጋጀው ስልጠና ትናንት ተጀምሯል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን እና የእንግሊዙ እግር ኳስ ማኅበር (FA) ያዘጋጁት የአሰልጣኞች ስልጠና በአዲስ አበባ ስታዲየም በመስጠት ላይ ይገኛል።

ስልጠናው የ36 የከፍተኛ ሊግ ዋና አሰልጣኞችን ያካተተ ሲሆን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ቴክኒክ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር አቶ መኮንን ኩሩ መርሐ ግብሩን በንግግር ከፍተዋል። የስልጠናው ዓላማ በእግርኳስ የጨዋታ እቅድ እንዴት ማውጣት እንዴት እንደሚቻልና ወጥነት ያለው የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ መፍጠር ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል። ስልጠናውን በሁለት ባለሞያዎች እንደሚሰጥም ማወቅ ተችሏል።

ስልጠናው በሁለት መርሀ ግብር የተከፈለ ሲሆን በጠዋት መርሀ ግብር የክፍል ውስጥ ትምህርት፤ በከሰዓቱ ደግሞ የሜዳ ላይ ተግባር የሚከናወን ይሆናል።

ለአምስት ቀን የሚቆየው ይህ ስልጠና በመጪው ዓርብ ሲጠናቀቅ ትናንት በነበረው የከሰዓት መርሀ ግብር ላይ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ጂራ በመገኘት ተከታትለዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ