ወላይታ ድቻ ከመስመር ተከላካዩ ጋር ተለያየ

የግራ መስመር ተከላካዩ ይግረማቸው ተስፋዬ ከወላይታ ድቻ ጋር ተለያይቷል፡፡

በአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ አማካኝነት በክረምቱ የዝውውር መስኮት በመስከረም ወር አጋማሽ ነበር ወላይታ ድቻን የተቀላቀለው የቀድሞው የሀዲያ ሆሳዕና እና ወልዲያ ተጫዋች ወደ ወላይታ ድቻ ካመራ በኋላ ጥቂት ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን ቀሪ የ18 ውል እየቀረው መለያየቱን ለማወቅ ተችሏል። ቡድኑ በዝውውር መስኮቱ በግራ ተከላካይ ስፍራ ላይ አበባው ቡጣቆን ማስፈረሙ የሚታወቅ ነው።

ፕሪምየር ሊጉ በመቋረጡ ምክንያት ለተወሰኑ ቀናት ለተጫዋቾቹ ዕረፍትን የሰጠው ወላይታ ድቻ ከዚህ ቀደም ከሁለት ተጫዋቾች ጋር መለያየቱ የሚታወስ ሲሆን አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረሙ ይታወሳል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ