ወልዋሎ አማካይ ለማስፈረም ተቃርቧል

ከወልዋሎ ጋር ልምምድ የጀመረው ፀጋአብ ዮሴፍ ወደ ክለቡ ለማምራት ተቃርቧል።

በውድድር ዓመቱ መጀመርያ ወደ ሲዳማ ቡና ፈርሞ ለሳምንታት ከቡድኑ ጋር ቆይታ ካደረገ በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ከቡድኑ ጋር የተለያየው ይህ ተጫዋች ላለፉት ቀናት ከወልዋሎ ጋር ልምምድ እየሰራ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም በይፋ ፌርማን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።

ከሀዋሳ ከተማ ታዳጊ ቡድን ወጥቶ ለአሳዳጊው ክለቡ ዋና ቡድን እና ፋሲል ከነማ መጫወት የቻለው ይህ አማካይ የፈጣሪ አማካይ እጥረት ላለባቸው ቢጫ ለባሾች ጥሩ ፊርማ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

በትናንትናው ዕለት ከሦስት ተጫዋቾች ጋር በስምምነት ለመለያየት የተስማሙት ወልዋሎዎች በቀጣይ ሳምንት ከሦስቱ ተጫዋቾች ጋር በይፋ ከተለያዩ በኋላ አማካዩን የግላቸው ያደርጋሉ።

© ሶከር ኢትዮጵያ