ሀዲያ ሆሳዕና ይግባኝ ጠየቀ

ከሰሞኑ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠንከር ያለ በዲሲፕሊን ኮሚቴ ቅጣት የተጣለበት ሀዲያ ሆሳዕና ይግባኝ ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 16ኛው ሳምንት በሜዳው መቐለ 70 እንደርታን አስተናግዶ 1ለ0 ሽንፈት ገጥሞት የነበረው ሆሳዕና በወቅቱ በጨዋታው ላይ የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት ታይቷል በማለት በክለቡ ላይ በዓመቱ ለሁለተኛ ጊዜ ቅጣት መጣሉ ይታወሳል፡፡ በቅጣቱ መሠረትም አምስት የሜዳውን ጨዋታ ከሜዳው ውጪ እንዲጫወት እና የ110 ሺህ ብር ቅጣት ተላልፏል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ክለቡ ቅጣቱ አግባብ አይደለም በሚል ባለ 3 ገጽ የይግባኝ ደብዳቤን ለፌዴሬሽኑ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ አቅርቧል፡፡

የደብዳቤው ዝርዝር👇

© ሶከር ኢትዮጵያ