ሀዋሳ ከተማ የቀድሞ ተጫዋቹን አስፈረመ

የግራ መስመር ተከላካዩ ደስታ ዮሀንስ ለቀድሞ ክለቡ ሀዋሳ ከተማ ፊርማውን አኑሯል፡፡

ለሀዋሳ ከተማ የታዳጊ ቡድን በመጫወት የክለብ ህይወትን ከጀመረ በኋላ በ2008 ወደ ዋናው ቡድን በማደግ እስከ 2011 ሀዋሳ ከተማን ያገለገለው ደስታ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ሀዋሳ ከተማን በመልቀቅ ወደ መከላከያ አምርቶ የነበረ ቢሆንም ብዙም ሳይቆይ ውሉን ያቋረጠ ሲሆን ባለፉት ወራት ከነበረበት ጉዳት አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ አገግሞ ዳግም አሳዳጊ ክለቡን በአንድ አመት ከስድስት ወራት ውል ተቀላቅሏል፡፡

ትላንት ከዕረፍት መልስ ልምምድ የጀመሩት ሀዋሳ ከተማዎች በቀጣዩ ቀናትም ተጨማሪ ተጫዋቾችን እንደሚያስፈርሙ የሚጠበቅ ሲሆን ረዳት አሰልጣኞችን ከቀናት በኋላ በይፋ እንደሚሾሙ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ