ሲዳማ ቡና የናይጄሪያዊውን ተከላካይ ዝውውር አጠናቀቀ

ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር በስምምነት ተለያይቶ የነበረው ናይጄሪያዊው ተከላካይ ላውረንስ ኤድዋርድ ለሲዳማ ቡና ፊርማውን አኖረ፡፡

የኢራቁን ክለብ አልካርባላን በመልቀቅ ነበር ከስድስት ወራት በፊት መቐለ 70 እንደርታን የተቀላቀለው። ናይጄሪያዊ የመሀል እና የግራ መስመር ተከላካይ ላውረንስ ኢድዋርድ አግቦር ከሁለት ሳምንት በፊት ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር የአምስት ወራት ኮንትራት እየቀረው በስምምነት መለያየቱ የሚታወስ ሲሆን ከሲዳማ ቡና ጋር በቅርቡ ስምምነት አስቀድሞ መፈፀም ከቻለ በኃላ በዛሬው ዕለት ለአንድ ዓመት በክለቡ ለመጫወት ፊርማውን ማኖሩን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ሲዳማ ቡና ነገ ከእረፍት መልስ ወደ ዝግጅት የሚመለስ ይሆናል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ