አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ወደ አሜሪካ አቅንቷል

በ2012 የውድድር ዘመን ኢትዮጵያ ቡናን ለማሰልጠን የተረከበው አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ወደ አሜሪካ አቅንቷል።

አነጋጋሪው አሰልጣኝ ለረዥም ዓመታት ወደኖረበት አሜሪካ ያቀናው ለቤተሰብ ጥየቃ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ትናንት ወደ ስፍራው የተጓዘው የአስራ አምስት ቀናት ቆይታ ለማድረግ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን ምን አልባትም የሊጉ ውድድር በተባለበት ቀን የማይጀምር ከሆነ ቆይታው ሊጨምር እንደሚችል ተገምቷል።

አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ በእስካሁኑ ቆይታው አጀማመራቸው መልካም የሚባል የነበረ ቢሆንም በኃላ ላይ የውጤት መገራገጭ አጋጥሟቸው በወራጅ ቀጠና ውስጥ ለመግባት ተገደው ቢቆዩም በአንደኛው ዙር የመጨረሻ ጨዋታ እና በሁለተኛው ዙር ባስመዘገቡት የተሻለ ውጤት በ22 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ቡድኑ እንዲገኝ አስችለዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ