ሀዋሳ ከተማ እና ተስፋዬ መላኩ ተለያዩ

በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሀዋሳ ከተማን ተቀላቅሎ የነበረው ተስፋዬ መላኩ በስምምነት ተለያይቷል፡፡

በአሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ከተፈጥሯዊ የተከላካይ ቦታው ይልቅ አብዛኛዎቹን ጨዋታዎች በአማካይ ስፍራ ላይ በመጫወት ያሳለፈው ተስፋዬ በአዲሱ አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት አማካኝነት ዓመቱን ይጨርሳል ተብሎ ቢጠበቅም ከክለቡ ጋር በፈጠረው ስምምነት መሠረት መለያየቱን ለማወቅ ተችሏል። በ17ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሀዋሳ ከተማ በሜዳው ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ነጥብ በተጋራበት ወቅት ከጨዋታው መጠናቀቅ ተከትሎ ከደጋፊዎቹ ጋር የገባው ሰጣገባ ለመለያየቱ መነሻ ስለመሆኑም ተሰምቷል።

© ሶከር ኢትዮጵያ