ሀዋሳ ከተማ ሁለተኛ ተጫዋቹን አስፈርሟል

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ዓባይነህ ፊኖ ሀዋሳ ከተማን ተቀላቅሏል፡፡

የቀድሞው የአዲስ አበባ ፖሊስ እና ኢኮሥኮ ተጫዋች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ኢኮሥኮን በመልቀቅ የፕሪምየር ሊጉ አዲስ አዳጊ ክለብ ወልቂጤ ከተማን በአንድ ዓመት ውል ተቀላቅሎ የመጀመሪያውን ዙር በክለቡ ካሳለፈ በኋላ በቅርቡ በስምምነት ተለያይቶ በአንድ ዓመት ውል ማረፊያውን ሀዋሳ ከተማ አድርጓል፡፡

ከተስፋዬ መላኩ ጋር በስምምነት በመለያየት ዓባይነህ ፊኖ እና ተከላካዩን ደስታ ዮሐንስን ያስፈረሙት ሀዋሳ ከተማዎች በቀጣዩ ቀናት ተጨማሪ አዳዲስ ተጫዋቾች እንደማያስፈርሙ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ