ፀጋአብ ዮሴፍ ሳይፈርም ቀርቷል

ከወልዋሎ ጋር ልምምድ ጀምሮ ይፈርማል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ፀጋአብ ዮሴፍ ሳይፈርም ቀርቷል።

ከቀናት በፊት ወደ ዓዲግራት አምርቶ ከወልዋሎ ጋር ልምምድ በመጀመር በጥቂት ቀናት ውስጥ ይፈርማል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው አማካዩ ፀጋአብ ዮሴፍ ዝውውሩ ባልታወቀ ምክንያት ተጨናግፏል። የውድድር ዓመቱ ከሲዳማ ጋር ጀምሮ ባልታወቀ ምክንያት ከቡድኑ ጋር የተለያየው ይህ የቀድሞ የፋሲል ከነማና የሀዋሳ ከተማ አማካይ በመጀመርያው ዙር ካለቡድን መቆየቱ ይታወሳል።

በዛሬው ዕለት ከካርሎስ ዳምጠው፣ ፍቃዱ ደነቀ እና ምስጋናው ወልደዮሐንስ ጋር በስምምነት ይለያያሉ ተብለው የሚጠበቁት ቢጫ ለባሾቹ በቀሩት የዝውውር ቀናት አንድ አማካይ ያስፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ