የኢትዮጵያ እግርኳስ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ?

የዓለም ስጋት በሆነው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተቋረጡት የኢትዮጵያ እግርኳስ ውድድሮች ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ከሰዓታት በኃላ ቁርጡ ይታወቃል።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ ማንኛቸውም ውድድሮች እስከ መጋቢት ወር መጨረሻ ድረስ እንደሚቋረጡ ፌዴሬሽኑ ከመንግስት ጋር ባደረገው ውይይት ማሳወቁን ተከትሎ ሙሉ ለሙሉ ውድድሮች መቋረጣቸው ይታወቃል። አሁን አሁን እየወጡ ባሉ መረጃዎች መሠረት ከሆነ በኢትዮጵያ በሽታውን መቆጣጠር እስኪቻል ድረስ ውድድሮች ላልተወሰኑ ቀናት ሊቋረጥ እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የእግርኳሱ የበላይ አካል የሆነው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የውድድሩን ቀጣይ እጣ ፈንታ አስመልክቶ ዝርዝር መረጃዎችን ለመስጠት ከደቂቃዎች በኋላ (09:00 ላይ) ወሎ ሰፈፍ በሚገኘው የፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠርቷል።

© ሶከር ኢትዮጵያ