ካርሎስ ዳምጠው በበጎ አድራጎት ተሳትፏል

ከቀናት በፊት ከወልዋሎ ጋር በስምምነት የተለያየው ግዙፉ አጥቂ ካርሎስ ዳምጠው ለሜሪ ጆይ የገንዘብ እና የኮሮና ቫይረስ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረጊያ ቁሳቁስ እርዳታ አድርጓል።

በዛሬው ዕለት ለእርዳታ ማኅበሩ የገንዘብ እና የወቅቱን ወረርሺኝ ለመከላከል የሚረዱ ቁሳቁሶች ድጋፉን ያደረገው ይህ ተጫዋች በቀጣይ ቀናትም ሌሎች ተመሳሳይ ድጋፎች እንደሚያደርግ የገለፀ ሲሆን ሰናይ ተግባሩም ክለቦች እና ሌሎች ተጫዋቾች እንዲከተሉት ጥቆማ አድርጓል።

በጉዳዩ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አጭር ቆይታ ያደረገው ካርሎስ ዳምጠው ለማኅበሩ እርዳታ ማድረጉ እንዳስደሰተው ገልጾ የእግር ኳስ ማኅበረሰቡ በዓለም ላይ ያጋጠመውን ወረርሺኝ ለመከላከል የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪውን አቅርቧል። “የበኩሌን በመወጣቴ ደስ ብሎኛል ፤ በቀጣይ ግዜያትም በዘርያዬ ያሉት ሌሎች ግለሰቦች በማስተባበር ተመሳሳይ ስራዎች እሰራለው።” ብሏል።

© ሶከር ኢትዮጵያ