ደስታ ጊቻሞ ስሑል ሽረ አምርቷል

ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር በስምምነት የተለያየው የመሐል ተከላካዩ ደስታ ጊቻሞ ወደ ስሑል ሽረ አምርቷል፡፡

የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን ጨምሮ በኢትዮጵያ መድን፣ ሻሸመኔ ከተማ እና ደቡብ ፖሊስ መጫወት የቻለው ይህ ተጫዋች በክረምቱ ወደ ሀዲያ ሆሳዕና አምርቶ የመጀመርያው ዙር አመዛኝ ጨዋታዎችን የተጫወተ ሲሆን በአዲሱ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ብዙም ተመራጭ አለመሆኑን ተከትሎ የአምስት ወራት ውል እየቀረው በስምምነት በመለያየት የስሑል ሽረ አራተኛ ፈራሚ በመሆን ተጉዟል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ