ወልዋሎዎች አማካይ ለማስፈረም ተቃርበዋል

ሄኖክ ገምቴሳ የአማካይ ክፍል ተጫዋች በማፈላለግ ላይ ወደሚገኙት ወልዋሎዎች ለማምራት ተቃርቧል።

ከዚህ በፊት በአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ሥር በፋሲል ከነማ እና ጅማ አባ ጅፋር የተጫወተው ሄኖክ ባቀረበው የመልቀቂያ ጥያቄ መሰረት ቀሪ የስድስት ወር ውል እያለው ከጅማ አባጅፋር ጋር መለያየቱ የሚታወስ ሲሆን ዝውውሩ በተሳካ ሁኔታ የሚያጠናቅቅ ከሆነ በርካታ አማካይ ላስፈረሙት ቢጫ ለባሾቹ ተጨማሪ ግብአት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ከወልዋሎ ጋር በተያያዘ ሌላ ዜና ከሁለተኛው ቡድኑ ተጫዋቾች ለማሳደግ እንቅስቃሴ እንደጀመረ ለማወቅ ተችሏል።

© ሶከር ኢትዮጵያ