ባህር ዳር ከተማ ከአማካይ ተጨዋቹ ጋር ተለያይቷል

በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት የጣናው ሞገዶቹ ዓምና ወደ ቡድናቸው ከቀላቀሉት የአማካይ መስመር ተጨዋቻቸው ጋር ተለያይተዋል።

ቡድኑን የለቀቀው ተጨዋች ሚካኤል ዳኛቸው ነው። ይህ ተጨዋች ከአንድ ዓመት በፊት በነበረው የግማሽ ዓመት የዝውውር መስኮት አውስኮድን ለቆ ባህር ዳርን መቀላቀሉ ይታወሳል። ተጨዋቹ ቡድኑን ከተቀላቀለ በኋላም በአሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው የመሰለፍ እድል ሳያገኝ በመቆየት በተጠባባቂ ወንበር ላይ በርከት ያሉ ጊዜያትን አሳልፏል። በዘንድሮ የውድድር ጊዜም ሚካኤል አዲሱን የክለቡ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን ማሳመን ተስኖት በተጠባባቂ ወንበር ላይ በመሆን ከክለቡ ጋር ቆይቷል።

ይሁን እና ተጨዋቹ ከክለቡ ጋር ለመቆየት የተስማማበት ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ ክለቡን እንዲለቅ ሆኗል።

© ሶከር ኢትዮጵያ